ህዝብና መንግስት የጣለብንን አደራ በታማኝነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን የፌደራል ፖሊስ የባህር ላይ እና ዳርቻዎች ጥበቃ አባላት ገለጹ።
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጋር በመተባበር በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚሰማሩ የባህር ላይና ዳርቻዎች ጥበቃ (costal guard) የፖሊስ ምልምል አባሎችን በመሰረታዊ ባህርተኝነት አሰልጥኖ አስመርቋል። ተመራቂዎች የግድቡን ደህንነት ከሌሎች የጸጥታ ሀይሎች ጋር ተቀናጅተው እንደሚሰሩ ተገልጿል።
ካነጋገርናቸው ተመራቂ የባህር ላይ እና ዳርቻዎች ጥበቃ አባላት መካከል ሳጅን ሙሉቀን አርጃ በስልጣው በቂ እውቀት እና ክህሎት መጨበጡን ገልጿል። ባገኘው ስልጠና መሰረትም ለሚሰጡት ግዳጆች መዘጋጀቱን ተናግሯል። የመንግስት እና የህዝብን አደራ በመሸከምም ኢትዮጵያን በታማኝነት ለማገልገል ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል።

ረዳት ሳጅን አማኑኤል ኪዳኔም ስልጠናው በቂ እውቀት የጨበጠበት መሆኑን ገልጾ፤ ለሚሰጡ ግዳጆች ዝግጁ መሆኑን ተናግሯል። ሳጅን መሰለች ማሻ እና ረዳት ሳጅን ሸጋዬ ተመስገን ከዚህ ቀደም በግዳጅ ላይ መቆየታቸውን ገልጸው፤ አሁንም ለላቀ ስራ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
አሁንም ህዝብና መንግስት የጣለባቸውን አደራ በብቃት ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል። በስልጠናው መሰረት የውሀ አካላትን እና ዳርቻዎች በተገቢው መንገድ እንደሚጠብቁ የገለጹት ደግሞ ረዳት ሳጅን እዩኤል ጌቱ እና ረዳት ሳጅን ክብሬ ውበቱ ናቸው።ባገኙት እውቀት እና ክህሎት መሰረትም የሚሰጣቸውን ተልእኮ በብቃት እንደሚወጡ ማረጋገጣቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡ህዝብና መንግስት የሰጣቸውን አደራ በጀግንነት እና በታማኝነት እንደሚወጡ ጠቁመዋል።