በትራምፕ የተጣሉ አብዛኛዎቹ ዓለም አቀፍ ታሪፎች ሕገ-ወጥ መሆናቸውን የአሜሪካ ፍርድ ቤት ፈረጀ

You are currently viewing በትራምፕ የተጣሉ አብዛኛዎቹ ዓለም አቀፍ ታሪፎች ሕገ-ወጥ መሆናቸውን የአሜሪካ ፍርድ ቤት ፈረጀ

AMN – ነሐሴ 24/2017 ዓ.ም

አብዛኛዎቹ በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የተላለፉ ዓለም አቀፍ ታሪፎች ሕገ-ወጥ ናቸው ሲል የአሜሪካው ፍርድ ቤት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

የፌዴራል ጉዳዮችን የሚመለከተው የአሜሪካ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በአብላጫ ድምጽ በወሰነው ውሳኔ፤ ታሪፉ የተጣለው ለአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ያልተለመዱ ስጋቶችን ለመከላከል የሚያስችል ስልጣን በሚሰጠው የአስቸኳይ የኢኮኖሚ ኃይል ሕግ መሠረት ነው ሲሉ ፕሬዚደንት ትራምፕ ያቀረቡትን መከራከሪያ ሃሳብ ከሕግ ጋር የሚጻረር፤ ዋጋ የሌለው ሲል ውድቅ አድርጎታል።

ለትራምፕ አስተዳደር ውሳኔውን ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የመውሰድ እድል ለመስጠት ሲባል የፍርድ ቤቱ ውሳኔ እስከ አውሮፓዊያኑ ጥቅምት 14 ድረስ ተግባራዊ እንደማይሆንም ተመላክቷል፡፡

ይህን ተከትሎም ትራምፕ የይግባኝ ሰሚውን ፍርድ ቤት ውሳኔ በትሩዝ ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ሲተቹም፤ ይህ ውሳኔ እንዲጸድቅ የሚፈቀድ ከሆነ አሜሪካን ይጎዳል፤ በፋይናንስም ደካማ ያደርጋታል እናም ጠንካራ መሆን አለብን ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ የተላለፈው ብይን ከታሪፎቹ በተጨማሪም ትራምፕ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ አደንዛዥ እፅ ለማስቆም ወሳኝ ነው ሲሉ በካናዳ፣ በሜክሲኮ እና በቻይና ላይ የጣሉትን ታሪፍ ውድቅ አድርጎታል።

ሆኖም ውሳኔው በተለያዩ የፕሬዚደንቱ ሥልጣን መሠረት የሚገቡ እንደ ብረትና አልሙኒየም ባሉ ቁሶች ላይ ተግባራዊ እንደማይሆን በዘገባው ተመላክቷል።

በአስማረ መኮንን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review