ቼልሲ የአልሃንድሮ ጋርናቾን ፊርማ ይፋ አደረገ

You are currently viewing ቼልሲ የአልሃንድሮ ጋርናቾን ፊርማ ይፋ አደረገ

AMN ነሃሴ 24/2017 ዓ.ም

ቼልሲ አሌሃንድሮ ጋርናቾን ከማንችስተር ዩናይትድ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል።

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ለ21 ዓመቱ አርጀንቲናዊ 40 ሚሊየን ፓውንድ ይከፍላል።

ለወደፊት ተጫዋቹን ከሸጠ ከሚያገኘው ትርፍ 10 በመቶ ለዩናይትድ ለመስጠት ተስማምቷል።

ጋርናቾ በቼልሲ ሰባት ዓመት የሚያቆየው ውል ፈርሟል።

ገና በ16 ዓመቱ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ማንችስተር ዩናይትድን የተቀላቀለው ጋርናቾ በቀይ ሰይጣናቱ ቤት አምስት ዓመት ቆይቷል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review