ሃይለማሪያም ኪሮስ የሲድኒ ማራቶንን ያሸነፈ ሁለተኛው ኢትዮጵያዊ ሆኗል።
ሃይለማርያም ርቀቱን ለማጠናቀቅ 2:06:06 ሰዓት ፈጅቶበታል። ሰዓቱ በአውስትራሊያ የተመዘገበ ፈጣኑ ሰዓት እንደሆነ ተነግሯል።
ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አዲሱ ጎበና 2:06:16 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል።
የሴቶቹን ውድድር ሲፈን ሃሰን በቀዳሚነት ጨርሳለች። ኔዘርላንዳዊቷ አትሌት በአውስትራሊያ ፈጣን የተባለውን 2:18:22 ሰዓት በማስመዝገብ አሸንፋለች።
በሸዋንግዛው ግርማ