የአዲስ አበባ መጅሊስን ለቀጣይ አምስት ዓመታት የሚመሩ ፕሬዚዳንት፣ ምክትል ፕሬዚዳንት እና ዋና ጸሀፊ ዛሬ ይፋ ይደረጋል።
5 ወራትን ያስቆጠረው የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የ2017 ምርጫ አስፈጻሚ ቦርድ የመጀመሪያውን ቅድመ ምርጫ ምዕራፍ በስኬት አጠናቋል፡፡
ነሐሴ 9 እና 11 በ334 መስጂዶች፣ ነሐሴ 18 በ119 ወረዳዎችና ነሐሴ 22 ደግሞ በ11 ክፍለ ከተሞች ፍጹም ሰላማዊ ምርጫ የተደረገ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለት አራተኛውና የመጨረሻው የምርጫ እርከን የሚካሄድ ይሆናል።
የ2017 የምርጫ አስፈጻሚ ቦርድ በመስጂድ፣ በወረዳና በክፍለ ከተማ ደረጃ ምርጫ ሲያካሂድ መቆየቱ ይታወቃል፡፡
በአዲስ አበባ ደረጃ የመጨረሻ የሆነውን የአዲስ አበባ መጅሊስ የሥራ አስፈጻሚዎችና የኦዲትና ኢንስፔክሽን ምርጫ እያካሄደ ሲሆን፣ ዛሬ ከሰዓት በኃላ የመጨረሻውን ተመራጭ የሆኑትንና የአዲስ አበባ መጅሊስን ለቀጣይ አምስት ዓመታት የሚመሩትን ፕሬዚዳንት፣ ምክትል ፕሬዚዳንት፣ ዋና ጸሀፊና የመጅሊሱን የስራ አስፈጻሚ አባላትን ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
በአንዋር አህመድ