የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ደጋፊዎች ማህበር በመዲናዋ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የፅዳት መርሐ ግብር አካሄደ

You are currently viewing የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ደጋፊዎች ማህበር በመዲናዋ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የፅዳት መርሐ ግብር አካሄደ

AMN- ነሐሴ 25/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ደጋፊዎች ማህበር በአዲስ አበባ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የፅዳት መርሐ ግብር አካሂዷል፡፡

በመርሐ ግብሩ የአዲስ አበባ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ዴሲሳ፣ አዲስ አበባን ፅዱ እና ውብ ከተማ ለማድረግ የማህበረሰብ አቀፍ ተቋማት ተሳትፎ ወሳኝ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ተቋማት በፅዳት ላይ የሚኖራቸውን ሚና ለማሳደግ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ደጋፊዎች ማህበር አስረኛ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ እየተንቀሳቀሱ ማጽዳት በሚል ስያሜ፣ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት የፅዳት መርሐ ግብር ማከናወኑን የማህበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አንዱዓለም ጌታቸው ገልፀዋል፡፡

አዲስ አበባ ላይ የጀመሩትን የፅዳት መርሐ ግብር አጠናክረው እንደሚቀጥሉና በተለይም ደግሞ ንቅናቄውን በክልል ከተሞችም እንደሚያካሂዱ የማህበሩ ዓባላት ተናግረዋል፡፡

በንጉሱ በቃሉ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review