ፕሬዚዳንት ፑቲን በሻንጋይ ትብብር ድርጅት ጉባኤ ለመታደም ቲያንጂን ከተማ ገቡ

You are currently viewing ፕሬዚዳንት ፑቲን በሻንጋይ ትብብር ድርጅት ጉባኤ ለመታደም ቲያንጂን ከተማ ገቡ

AMN- ነሐሴ 25/2017 ዓ.ም

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በህዝብ ብዛት ከዓለም ትልቁን ድርሻ የሚወስዱ 20 ሀገራት በሚሳተፉበት በሻንጋይ ትብብር ድርጅት ጉባኤ ለመታደም ቻይና ቲያንጂን ከተማ ገብተዋል፡፡

በፈረንጆቹ 2001 ላይ በቻይና፣ ሩሲያ፣ ካዛኪስታን ፣ ኪርጊስታን፣ ታጃኪስታን እና ኡዝቤክስታን የተመሠረተው ጉባኤው፣ ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ መካከለኛው እስያ ላይ ያደርግ የነበረውን ትኩረት በመቀየር ዓለም አቀፍ ጉዳዮችን የሚነጋገርበት መድረክ ሆኗል፡፡

ጉባኤው የዓለማችን ሁለተኛዋ ልዕለ ኃያል ሀገር ቻይና ከአሜሪካ መራሽ ዓለም አቀፍ ሥርዓት ወጣ ባለ መልኩ ለዓለም አቀፍ ትብብር እና ምክክር ዕድል እንደፈጠረላት ይገለፃል፡፡

የጉባኤው ተሳታፊ ሀገራት ከድንበር ጋር የተገናኘ ውስብስብ ችግር ያለባቸው መሆኑም ይገለፃል፡፡

ለአብነትም ህንድ ከፓኪስታን፣ ህንድ ከቻይና፣ ሳዑዲ አረቢያ ከኢራን እንዲሁም መካከለኛው እስያ ከቻይና እና ሩሲያ ጋር ድንበር ነክ ችግር እንዳለባቸው ይታያል፡፡

ከዛሬ የሚጀምረው የሻንጋይ ትብብር ድርጅት ጉባኤ ለሁለት ቀናት የሚካሄድ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ፕሬዚዳንት ፑቲን ከትራምፕ ጋር በአላስካ ከተገናኙ በኋላ፣ ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂን ፒንግ ጋር ለመገናኘት ዕድል እንደፈጠረላቸው የአልጀዚራ እና ሲጂቲኤን ዘገባ ያመለክታል፡፡

በማሬ ቃጦ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review