ለነገዋ የሴቶች የተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል 810 ሰልጣኞችን አስመረቀ

You are currently viewing ለነገዋ የሴቶች የተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል 810 ሰልጣኞችን አስመረቀ

AMN- ነሐሴ 25/2017 ዓ.ም

ለነገዋ የሴቶች የተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል የ3ኛ ዙር 810 ሰልጣኞችን አስመረቀ

ተቋሙ ከተመሠረተ ግዜ ጀምሮ በሶስት ዙር 1 ሺህ 692 ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች የተጋለጡ ሴቶችን በተለያዩ የሞያ መስኮች በማሰልጠን ወደ ስራ አሰማርቷል።

በሶስተኛ ዙር ተቋሙ ከተቀበላቸው ሴት ሰልጣኞች መካከል 626 በመደበኛ 184 ደግሞ በተመላላሽነት የሰለጠኑ 810 ሰልጣኞችን ነው ያስመረቀው።

ተመራቂዎቹ ለአንድ ወር የተሃድሶ ስልጠና እንዲሁም ለአራት ወራት የሞያ ክህሎት ስልጠናን ከወሰዱ በኋላ፣ በተቋም ደረጃ የተሰጠውን ምዘና በብቃት ያለፉ እና በከተማ ደረጃ የሚሰጠውን የብቃት ማረጋገጫ ምዘና ወስደው 95 በመቶ እና ከዛ በላይ ውጤት ያመጡ መሆናቸው ተገልጿል።

ተመራቂዎቹ በሙሉ በመንግስት እና በተለያዩ ባለሀብቶች እና ተቋማት የስራ እድል የተመቻቸላቸው መሆኑም ተገልጿል።

በሰብስቤ ባዩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review