ሸይኽ ሱልጣን አማን ኤባ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤትን ለቀጣይ አምስት አመታት በፕሬዚዳንትነት እንዲመሩ ተመረጡ

You are currently viewing ሸይኽ ሱልጣን አማን ኤባ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤትን ለቀጣይ አምስት አመታት በፕሬዚዳንትነት እንዲመሩ ተመረጡ

AMN- ነሐሴ 25/2017 ዓ/ም

ሸይኽ ሱልጣን አማን ኤባ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤትን ለቀጣይ አምስት አመታት በፕሬዚዳንትነት እንዲመሩ ተመርጠዋል።

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የ2017 የመጨረሻውን ምዕራፍ የመጅሊስ ምርጫ አጠናቋል።

5 ወራትን ያስቆጠረው የ2017 መጅሊስ ምርጫ አስፈጻሚ ቦርድ የመጀመሪያውን ቅድመ ምርጫ ምዕራፍ በስኬት ማጠናቀቁ የሚታወስ ሲሆን፣ በ334 መስጂዶች፣ በ119 ወረዳዎችና በ11 ክፍለ ከተሞች ፍጹም ሰላማዊ ምርጫ ሲያካሂድ ቆይቷል።

በአዲስ አበባ ደረጃ የመጨረሻ የሆነውን የአዲስ አበባ መጅሊስ የሥራ አስፈጻሚዎች፣ የኦዲትና ኢንስፔክሽን ምርጫ ያካሄደ ሲሆን፣ ዛሬ ከሰዓት በኃላ በተደረገውና የመጨረሻው በሆነው የምርጫ ሂደት የአዲስ አበባ መጅሊስን ለቀጣይ አምስት ዓመታት የሚመሩ ፕሬዚዳንት፣ ምክትል ፕሬዚዳንት ፣ ዋና ጸሀፊ እና የመጅሊሱን የስራ አስፈጻሚ አባላትን ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት፡-

-ሸይኽ ሱልጣን አማን ኤባ በከፍተኛ ድምጽ መጅሊሱን በፕሬዚዳንትነት እንዲመሩ ተመርጠዋል።

-ሸይኽ ሙሐመድ ሸሪፍ ደግም በምክትል ፕሬዚዳንትነት እንዲመሩ የተመረጡ ሲሆን፣ ሼሀቡዲን ኑራን ደግሞ ዋና ጸሀፊ ሆነዋል።

የአዲስ አበባ መጅሊስ ስራ አስፈፃሚዎችንም ይፋ ያደረገ ሲሆን፣ በዚህም፡-

-ሸይኽ ሱልጣን አማን ኤባ

-ሸይኽ ሙሐመድ ሸሪፍ

-ሸይኽ ሁሴን ሰይድ

-ኡስታዝ ጋሊ አባቦሩ

-ሸይኽ ዙቤር ሬድዋን

-ሸይኽ ኑሩ ሑሴን ሙስጠፋ

-ኡስታዝ ሰላሃዲን መለስን በመምረጥ አጠናቋል።

በአንዋር አህመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review