የአዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት ከወዲሁ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ

You are currently viewing የአዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት ከወዲሁ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ

AMN- ነሐሴ 25/2017 ዓ/ም

በመዲናዋ መጪውን የአዲስ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት ከወዲሁ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሀብተየስ ዲሮ ገልጸዋል፡፡

ለዚህም ክልል ከሚገኙ አምራች ህብረት ስራ ማህበራት ጋር በቅንጅትና በትስስር እየተሰራ መሆኑን ምክትል ኮሚሽነሩ ገልጸዋል ።

ዩኒየኖች በበኩላቸው፣ ለአዲስ ዓመት የእርድ ሰንጋዎችን ጨምሮ የግብርና ምርቶችን ትስስር ከፈጠሩባቸው አምራች ማህበራት ጋር ግዥ እየፈጸሙ መሆኑን ገልፀዋል ። የአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን ትስስር ከፈጠረላቸው የክልል አምራቾች ጋር የምርት አቅርቦት ምልከታ አድርገዋል።

በምልከታውም የአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነሮችና የ11ዱም ዩኒየኖች የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።

በአዳማ፣ በወንጂ እና አካባቢው የእርድ ሰንጋዎችን ጨምሮ እንቁላልና ዱቄት አቅርቦትን የተመለከቱት ዩኒየኖቹ፣ የሸማቹን ማህበረሰብ ፍላጎትና አቅም ታሳቢ ባደረገ ተመጣጣኝ ዋጋ ግዥ መፈጸማቸውን ለኤ ኤም ኤን ተናግረዋል።

በቀጣይም ምርቶቹን በስፋት ወደ ከተማዋ በማስገባት በሸማች ማህበራት ሱቆች አማካኝነት ተደራሽ እንደሚሆኑ ነው የገለጹት ።

የገበያ ትስስሮችን በመፍጠር ምርት የማስገባት ስራዎች ቀደም ሲል መጀመራቸውን የገለፁት ምክትል ኮምሽነሩ ይሄው ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በቀጣይ ቀናቶችም ከሌሎች ክልሎች ምርት የማስገባት ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።የምርት አቅርቦት ትስስሩ የበዓል ገበያን የተረጋጋ ለማድረግ የሚያስችል እንደሆነም ተመላክቷል።

በፍቃዱ መለሰ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review