ማንችስተር ሲቲ 100ኛ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታውን ባደረገው ኤርሊንግ ሃላንድ ግብ መምራት ቢችልም ውጤቱን አላስጠበቀም።
ለብራይተን ጀምስ ሚልነር በፍፁም ቅጣት ምት እንዲሁም ብርያን ግሩደ አስቆጥረዋል። የቀድሞ የማንችስተር ሲቲ እና ሊቨርፑል ተጫዋች ሚልነር በፕሪምየር ሊጉ ታሪክ በእድሜ ትልቁ (39 ዓመት 239 ቀናት) ፍፁም ቅጣት ምት አስቆጣሪ ሆኗል።
ሲቲ ካደረጋቸው ሦስት ጨዋታዎች ሦስት ነጥብ ብቻ አግኝቷል። በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገ ሌላ ጨዋታ ኖቲንግሃም ፎረስት በዌስትሃም ዩናይትድ 3ለ0 ተሸንፏል።
የለንደኑ ክለብ የውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ድሉን አግኝቷል። ለዌስትሃም ጃሮድ ቦዌን ፣ ሉካስ ፓኬታ በፍጹም ቅጣት ምት እንዲሁም ካሉም ዊልሰን አስቆጥረዋል።
በሸዋንግዛው ግርማ