የመጸዳጃ ቤት ፍሳሽ በመልቀቅ አካባቢውን የበከለ ተቋም 400ሺህ ብር ተቀጣ

You are currently viewing የመጸዳጃ ቤት ፍሳሽ በመልቀቅ አካባቢውን የበከለ ተቋም 400ሺህ ብር ተቀጣ

AMN-ነሃሴ 25/2017 ዓ/ም

የመጸዳጃ ቤት ፍሳሽ በመልቀቅ አካባቢውን የበከለ ተቋም 400ሺህ ብር መቀጣቱን የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታወቀ።

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 የሚገኘዉ አማዱ ሆቴል የሆቴሉን መፀዳጃ ቤት ፍሳሽ በመልቀቅ አካባቢውን በመበከሉ 400 ሺህ ብር መቅጣቱን ባለስልጣኑ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በላከዉ መረጃ አስታውቋል።

ድርጅቱ የመፀዳጃ ቤት ፍሳሽ ከሴፍቲ ታንኬር በቱቡ ወደ ውሃ መውረጃ በማገናኘት አካባቢው መበከሉን ነዉ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የገለጸዉ።

ግለሰቦችና ተቋማት ከእንደዚህ ዓይነት ድርጊቶች እንዲቆጠቡ ያሳሰበ ሲሆን ደንብ በሚተላለፉት ላይ የሚወስደውን እርምጃም ተጠናክሮ ይቀጥላል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review