አክሞንሊንክ ኮሌጅ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በዲፕሎማ በድግሪ እና በሁለተኛ ድግሪ ሲያስተምራቸውን ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡
በምረቃ መረሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልግሎት ኃላፊ እና የዕለቱ የክብር እንግዳ እዮብ አየነው (ዶ/ር) በምንኖርበት የውድድር ዓለም አሸናፊ ሆኖ ለመገኘት በተማሩበት የትምህርት ዘርፍ ብቁና ተወዳዳሪ ሆኖ መገኘት እደሚገባ አንስተዋል።
ተመራቂዎችም በተማሩበት የትምህርት ዘርፍ ሃገራቸውን በቁርጠኝነት ማገልገል እንደሚገባቸዉም መልእክት አስተላልፈዋል ፡፡
መንግስት ባለፉት የለውጥ ዓመታት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሄደበት ርቀት ያሚደነቅ መሆኑን የገለፁት የአክሞንሊንክ ኮሌጁ ፕሬዝዳንት ተሻለ ጌጡ (ዶ/ር) ኮሌጃቸው ተግባርን ያዋሃደ ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት እየሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ መንግስት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በሚያደርገው ጥረት የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሚና የላቀ መሆኑ ገልፀው ኮሌጁ በአዲሱ የትምርት ፖሊሲ መሰረት በመደራጀት ብቁና ተወዳዳሪ የሰለጠነ የሰው ሀይል በማፍራት ሀገራዊ ግዴታውን ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ኮሌጁ በመማር ማስተማር ተግባር በተጨማሪ ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ተልዕኮዎች ላይ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ማህበራዊ ሀላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን ነው ዶ/ር ተሻለ ጌጡ የገልፁት፡፡
ተመራቂዎች በበኩላቸው በንድፈ ሃሳብ እና በተግባር ባገኙት ዕውቀት ያስተማራቸውን ማህበረሰብ እና ሀገራቸውን ለማገልግል ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በታምሩ ደምሴ