ማንችስተር ዩናይትድ አንቶኒን ለሪያል ቤቲስ ለመሸጥ ተስማምቷል፡፡ የ25 ዓመቱ ብራዚላዊ የተጠናቀቀውን የውድድር ዓመት አጋማሹን በሪያል ቤቲስ በውሰት ማሳለፉ ይታወሳል፡፡
አሁን በቋሚ ዝውውር ወደ ስፔኑ ክለብ አምርቷል፡፡ ዩናይትድ ከዝውውሩ 25 ሚሊየን ዩሮ እንደሚያገኝ ዘ አትሌቲክ ዘግቧል፡፡ ሪያል ቤቲስ ለወደ ፊት ተጫዋቹን ከሸጠ ከትርፉ 50 በመቶ ለዩናይትድ ለመስጠት ተስማምቷል፡፡
ማንችስተር ዩናይትድ አንቶኒን በ2023 ነበር ከአያክስ በ82 ሚሊየን ፓውንድ የክለቡ ሁለተኛው ውዱ ተጫዋች በማድረግ ወደ ኦልድትራፎርድ ያመጣው፡፡
በሸዋንግዛው ግርማ