በአፍጋኒስታን በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ የሟቾች ቁጥር 610 ደረሰ

You are currently viewing በአፍጋኒስታን በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ የሟቾች ቁጥር 610 ደረሰ

AMN – ነሐሴ 26/2017 ዓ.ም

የአፍጋኒስታን ምስራቃዊ ክፍል በሬክተር ስኬል 6 በሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መመታቱን ተከትሎ የሟቾች ቁጥር በትንሹ 610 ደርሷል፡፡

በአደጋው ህይወታቸውን ካጡ በተጨማሪ የተጎዱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 300 መድረሱንም የሃገሪቱ መንግስት ቃል አቀባይ ገልፃዋል፡፡ በሬክተር ስኬል 6 የተመዘገበው የመሬት መንቀጥቀጥ 8 ኪሎ ሜትር ጥልቀት እንዳለዉ ተነግሯል።

ከአደጋው ከቆይታዎች በኋላም በድጋሚ በሬክተር ስኬል 4.5 የሆነ መሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱንም አልጀዚራ ዘግቧል፡፡ እንደ ዘገባዉ ከሆነ በአካባቢው የተገነቡ ቤቶች ጥንካሬ የሌላቸው በመሆናቸው አደጋውን አስከፊ እንዳደረገው እና ከዚህ ጋር ተያይዞ የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ ይችላል ነው የተባለው።

የመሬት መንቀጥቀጡ የመሬት መንሸራተት ሊያስከትል እንደሚችልም ባለሞያዎች አስጠንቅቀዋል፡፡ አደጋው ከካቡል እስከ ፓኪስታን ዋና ከተማ ኢስላማባድ በ300 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ያሉ ሕንፃዎችን ማናወጡም ተነግሯል።

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review