ህዝበ ሙስሊሙ የመውሊድን በዓል ሲያከብር የተቸገሩትን በማገዝ እና ስለሰላም በመስበክ ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ

You are currently viewing ህዝበ ሙስሊሙ የመውሊድን በዓል ሲያከብር የተቸገሩትን በማገዝ እና ስለሰላም በመስበክ ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ

AMN – ነሐሴ 26/2017 ዓ.ም

ህዝበ ሙስሊሙ የመውሊድን በዓል ሲያከብር የተቸገሩትን በማገዝ እና ስለሰላም በመስበክ ሊሆን እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

1ሺ 500ኛው የነብዩ መሀመድ ልደት(መውሊድ) በዓል በተለያዩ ሃይማኖታዊ መርሃ ግብሮች እንደሚከበር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 1ሺ 500ኛውን የነብዩ መሀመድ ልደት(መውሊድ) በዓል አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር የነብዩ መሀመድን ፈለግ በመከተል፤ የተቸገሩን በማገዝና ስለሰላም በመስበክ ሊሆን እንደሚገባ በመግለጫው ተመላክቷል።

ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር እርሳቸው ይመክሯቸው የነበሩ ሁለንተናዊ እሴቶችን ማለትም ሰላምን፣ መቻቻልን፣ ከሌሎች ጋር ተከባብሮ የመኖር እና የአንድነት እሴቶችን ሊያስታውስ ይገባልም ተብሏል።

የነቢዩ መሀመድ ልደት(መውሊድ) በዓል ሀሙስ በታላቁ አንዋር መስጅድ በተለያዩ ሀይማኖታዊ መርሃ ግብሮች እንደሚከበርም በመግለዉጫዉ ተጠቅሷል፡፡

በአንዋር አህመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review