በትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን የፌዴራል መንግስት በመደበው 483 ሚሊዮን ብር በጀት የንጹህ መጠጥ ውሀ ግንባታ ፕሮጀክት ተጀመረ።
በወረዳው የሚገነባው የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) እና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ ዛሬ ተቀምጧል።
የውሃ ፕሮጀክቱ በወረዳው በጅጅቐ፣ ስምረትና ፀይቀም ገጠር ቀበሌዎች ከ30 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል።
በፕሮጀክት ግንባታውም 58 ኪሎ ሜትር የውሀ መስመር ዝርጋታ፣ 56 የውሃ ማከፋፈያ ጣቢያዎች፣ አራት የማጠራቀሚያ ጋኖችና ስድስት የእንስሳት ማጠጫ ቦታዎች መካተታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ግንባታውም በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃም በወቅቱ ተጠቁሟል።