በምዕራብ ሱዳን ራቅ ብለው በሚገኙ የማራ ተራራዎች ላይ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ በትንሹ የ1 ሺህ ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነግሯል፡፡
ለቀናት የጣለው ከባድ ዝናብ ለመሬት መንሸራተቱ መንስኤ መሆኑን አካባቢውን የተቆጣጠረው የሱዳን ነፃ አውጪ ሃይል አስታውቋል።
ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ለሌሎች ቀጣናዊና ዓለም አቀፍ ተቋማትም የሰብአዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።
በፈረንጆቹ 2023 በሱዳን ዳርፉር ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ ከመኖሪያችው የተፈናቀሉ በርካታ ሱዳናውያን በማራ ተራራማ አካባቢዎች ተጠልለው መቆየታቸውን ቢቢሲ አሰነብቧል።
በሊያት ካሳሁን