የሀገርን እድገት በእውቀት እና ክህሎት በተገነባ ትውልድ እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ 32ኛው የትምህርት ጉባኤ የመዝጊያ መርሐ-ግብር በአድዋ ድል መታሰቢያ እየተደረገ ነው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) የተማሪዎችን ውጤታማነት ማላቅ፣ የመምህራንን አቅም መገንባት እና ቅንጅታዊ አሰራርን በማጉላት በእወወቀት እና ክህሎት የበቃ ምክንያታዊ ትውልድን ለመገንባት በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ ዓለም በደረሰበት ደረጃ ልክ በአዲስ አበባ ዘመናዊ ጉዞም እኩል የዘመኑ ለመማር ማስተማር ምቹ ከባቢን ለመፍጠር ከቀዳማይ ልጅነት ጀምሮ በየደረጃው በትኩረት እየተሰራበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የትምህርት ተደራሽነትን ማስፋት፣ ጥራትን ማላቅ እና መሰል ስራዎች የትኩረት ማዕከል እንደሚሆኑም ዶክተር ዘላለም ተናግረዋል፡፡ በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄን ጨምሮ የትምህርት ስርዓቱ የሚዘምንበትን ሁኔታ ማጠናከር፣ የትምህርት ቤት ምገባን በማጠናከር እጅ አጠር ዜጎችን የመደጎሙ ስራ በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ 32ኛው ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ በበጀት አመቱ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ተማሪዎችና ተቋማት ዕውቅና በመስጠት ተጠናቋል፡፡
በተመስገን ይመር