የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በመጪው ቅዳሜ ሴፕቴምበር 6/2025 ወይም ጳጉሜን 1/2017 ዓ.ም በካናዳ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አጀንዳ የሚያሰባስብበት መድረክ እንደሚያካሄድ አስታወቀ።
ኮሚሽኑ በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አጀንዳቸውን እያደራጁ እንዲጠብቁ ከወዲሁ ጥሪዉን አቅርቧል።
ሰፕቴምበር 6/2025 በካናዳ ቶሮንቶ በሚካሄደው በዚህ መድረክ በአካባቢው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ እንዲሳተፉ ጥሪ ማቅረቡን ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በላከዉ መረጃ አስታዉቋል።