ሁለተኛው ሀገር አቀፍ የኪነጥበብ እና የፈጠራ ውድድር በብሔራዊ ትያትር በመካሄድ ላይ ነው

You are currently viewing ሁለተኛው ሀገር አቀፍ የኪነጥበብ እና የፈጠራ ውድድር በብሔራዊ ትያትር በመካሄድ ላይ ነው

AMN – ነሐሴ 28/2017 ዓ.ም

ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚካሄደው ሁለተኛው ሀገር አቀፍ የኪነጥበብ፣ ስነጥበብና ፈጠራ ውድድር “ጥበብ ለኢትዮጵያ ማንሠራራት ብስራት” በሚል መሪ ሀሳብ በብሔራዊ ትያትር መካሄድ ጀምሯል።

በመርሐ-ግብሩ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሚኒስትር ሙሀዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ነብዩ ባዬ (ረ/ፕ) እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በመድረኩም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሚኒስትር ሙሀዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ ይህ ወቅት ከወቀሳ ወደ ሙገሳ የምንሸጋገርበት ወቅት ነው ብለዋል።

የህዳሴ ግድቡ ድል የኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንድ ውጤት በመሆኑ የኪነጥበቡ ዘርፍም ይህንን መነሻ በማድረግ ለኢትዮጵያ ማንሰራራትና መነሳሳት የሚሆኑ ስራዎችን በመስራት የበኩሉን ማበርከት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ በበኩላቸው፣ ጥበብ በመድረክ ዝግጅት ብቻ የሚወሰን ሳይሆን የሀገርን ገፅታ ለመገንባት የምንጠቀመው የዲፕሎማሲ መሳሪያ ነው ብለዋል።

ዝግጅቱ የሀገራችን የጥበብ ዘርፍ እምቅ አቅምን ለማሳየትና ተተኪ ባለሙያዎችን ለማፍራት የሚደረግ መሆኑንም ነው ሚኒስትሯ ያነሱት።

የኪነጥበብ ባለሙያዎችም በሚከውኗቸው የጥበብ ስራዎች ህብረብሔራዊ አንድነትን የሚያጠናክሩ የጥበብ ውጤቶችን መስራት እንደሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል።

በታምሩ ደምሴ እና በአይናለም አባይነህ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review