ፍትሃዊ የግብር አሰባሰብ ሥርዓትን ለማስፈን የሚያስችሉ አዳዲስ አሠራሮች መዘርጋቱን ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ

You are currently viewing ፍትሃዊ የግብር አሰባሰብ ሥርዓትን ለማስፈን የሚያስችሉ አዳዲስ አሠራሮች መዘርጋቱን ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ

AMN- ነሐሴ 28/2017 ዓ.ም

ፍትሃዊ የግብር አሰባሰብ ሥርዓትን ለማስፈን የሚያስችሉ አዳዲስ አሠራሮች መዘርጋቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው የአዲስ አበባን ገቢ አሠራር ለማዘመን በተከናወኑ ተግባራት ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫውም በግብር አሰባሰብ ላይ የሚከሰቱ ብልሹ አሰራሮችን በመቅረፍ በርካታ መዋቅራዊ አሠራሮችን መዘርጋቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ተናግረዋል፡፡

በግብር ከፋዩ ዘንድም ግልጸኝነትን ለመፍጠር የሚያስችል በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር መዘርጋቱንና በዚህም ተቋማዊ አቅም መፈጠሩን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ከታክስ አሰባሰብ ጋር ተያይዞ ከሐምሌ ወር ጀምሮ የቁጥጥር ሥራዎች እየተሠሩ ናቸው ያሉት ዳይሬክተሩ፤ በሠራተኞችም ዙሪያ የአሰራር ለውጥ እንዲመጣ ሰፋፊ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል።

የቢሮውን የሠው ኃይል አገልግሎት አሠጣጥ ለማዘመን ተከታታይ የግንዛቤ ማሳደግ ሥራዎች መሠራታቸውን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ፤ በአጠቃላይ 24 የሚደርሱ አዳዲስ ተቋማዊ አሠራሮች መዘርጋታቸውንም ተናግረዋል።

ቢሮው አስቀድሞ በዘረጋቸው አዳዲስ አሰራሮችም በሚፈጠሩት ምቹ ሁኔታዎች በ2018 በጀት ዓመት የተሻለ ገቢ ለመሠብሰብ መታቀዱንም ተናግረዋል።

በአለሙ ኢላላ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review