ህዝበ ሙስሊሙ የነብዩ መሀመድ መውሊድ በዓልን ሲያከብር የእሳቸውን አስተምህሮ ተግባራዊ በማድረግ ሊሆን እንደሚገባ ተጠቆመ

You are currently viewing ህዝበ ሙስሊሙ የነብዩ መሀመድ መውሊድ በዓልን ሲያከብር የእሳቸውን አስተምህሮ ተግባራዊ በማድረግ ሊሆን እንደሚገባ ተጠቆመ

AMN- ነሐሴ 29/2017 ዓ.ም

ህዝበ ሙስሊሙ የነብዩ መሀመድ መውሊድ በዓልን ሲያከብር የሳቸውን አስተምህሮ ተግባራዊ በማድረግ እና ለሀገር ሰላምና አንድነት በዱዓና በተግባር በማገዝ ሊሆን እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

1 ሺህ 500ኛው የነብዩ መሀመድ ልደት (መውሊድ) በዓል በታላቁ አንዋር መስጂድ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል፡፡

በበዓሉ ላይም የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ተወካይ ሼህ ፈትሁዲን ሼህ ዘይኑ ሙቀና፣ ህዝብ ሙስለሙ የነብዩ መሀመድ መውሊድ በዓልን ሲያከብር የሳቸውን አስተምህሮ ተግባራዊ በማድረግና ለሀገር ሰላምና አንድነት በዱዓና በተግባር በማገዝ ሊሆን እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በበዓሉ በታላቁ አንዋር መስጂድ በነሽዳ፣ በመንዙማ፣ በቁርዓን እንዲሁም በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡

በመርሐ-ግብሩ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ የእምነቱ አባቶችና ተካታዮች ታድመዋል፡፡

በአንዋር አህመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review