ለዘመን መለወጫ በዓል በቂ የምርት አቅርቦት መኖሩን የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ አስታወቀ

You are currently viewing ለዘመን መለወጫ በዓል በቂ የምርት አቅርቦት መኖሩን የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ አስታወቀ

AMN- ነሐሴ 29/2017 ዓ.ም

ለ2018 አዲስ ዓመት የከተማዋ ነዋሪ ምርቶችን ተረጋግተው መግዛት እንዲችሉ ዝግጅት መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ነዋሪው የሚፈልገውን ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ መግዛት እንዲችል ዘጠኝ የመንግስት የገበያ ማዕከላት፣ 219 የቅዳሜ እና እሁድ ገበያዎች፣ 20 ባዛሮችን ጨምሮ በየአካባቢው መደበኛ ያልሆኑ የበግና የፍየል የግብይት ቦታዎች ስለመዘጋጀታቸውም ኃላፊዋ ገልፀዋል።

ለበዓሉ መድረኮችን በማዘጋጀት የተለያዩ የነጋዴ አደረጃጀቶች፣ ህብረት ስራ ማህበራት፣ የኢንዱስትሪ አምራቾችና የክልል አርሶ አደሮች ጋር በመወያየት በቂ ምርት እንዲያቀርቡ መግባባት ላይ ስለመደረሱም አንስተዋል።

ቢሮው ለበዓሉ ህገወጥ የምርት ክምችት፣ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ፣ ህገ ወጥ የምርት ዝውውር እና የሚዛን ትክክልኛነትን የማረጋገጥ፣ የክትትልና ቁጥጥር ስራ እንደሚሰራም ተናግረዋል።

በፂዮን ማሞ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review