የነቢዩ መሐመድ ልደት በዓል (መውሊድ) በእስልምና እምነት ትልቅ ቦታ የሚሰጠው በዓል ሲሆን፣ በዓለም ዙሪያም በተለየ መልኩ ይከበራል።
ይህ ልዩ በዓል የእስልምናን ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች በሚያንጸባርቅ መልኩ የሚከበር ሲሆን፣ በዓለም ዙሪያ እንደየሀገራቱ ባሕላዊ ሁኔታ ይለያያል፡፡ በዓለም አብዛኛው የእስልምና እምነት ተከታዮች የመውሊድ በዓልን በልዩ ድምቀት ያከብራሉ፡፡ በመካከለኛው ምስራቅ እና በሰሜን አፍሪካ በዓሉ በልዩ ልዩ ሥነ ስርዓቶች ይከበራል፡፡
በሊባኖስ የእምነቱ ተከታዮች በመሰባሰብ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች ይከበራል፡፡ በግብፅ የመውሊድ በዓል አማኞች ተሰባስበው በድምቀት የሚያከብሩ ሲሆን፣ በሞሮኮ በሰልፍ፣ በሃይማኖታዊ ዝማሬና አስተምህሮ ያከብራሉ። በአልጄሪያ በባህላዊ ሥነ ሥርዓቶችና በሃይማኖታዊ ዝግጅቶች ሲከበር፣ በሶሪያ በሃይማኖታዊ መሰባሰብ እና ማራኪ ሰልፎች በሰፊው ይከበራል፡፡
በኢራቅ፣ በኦማን እና በፍልስጤም በዓሉ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ-ስርዓቶች እና ስብከቶች ማክበር የተለመደ ነው። ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራትም በዓሉ በልዩ ድምቀት ይከበራል፡፡
በሱዳን፣ በሞሪታኒያ፣ በሴኔጋል እና በናይጄሪያ የእምነቱ ተከታዮች ተሰባስበው በተለያዩ ሃይማኖታዊ ክዋኔዎች ያከብሩታል፡፡ በእስያ፣ በአውሮፓ እና በሰሜን አሜሪካም እንደየአካባቢዎቹ ሁኔታ የእምነቱ ተከታዮች መውሊድን በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ ስርዓቶች እንደሚያከብሩት የቁርአን ፎሬቨር መረጃ ያመለክታል፡፡
በታምራት ቢሻው