ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት እየተከናወኑ ባሉ እና በቀጣይ በሚሠሩ ተግባራት ላይ ገለጻ አድርገዋል።
በገለጻቸውም፤ እያከናወንነው ባለው ተግባር በአፍሪካ የነበረን ከተማ አፍርሶ ልዩ ከተማ የማድረግን ጅማሮ አሳይተንበታል ብለዋል። የኮሪደር ልማት ሥራው በሁሉም ከተሞች ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

ሕዝባችን ለመለወጥ፣ ለማደግ፣ ለመዘመን እና የተሻለ አካባቢ ለመፍጠር የሚከፈለውን ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ መሆን አለበት ብለዋል።
በዋዛ ፈዛዛ የምናሳካው ነገር የለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ደክመን፣ ሠርተን፣ ወጥተን ወርደን ሀገራችንን ሠርተን ልጆቻችን የተሻለች ሀገር እንዲረከቡ ማድረግ ከሁላችንም የሚጠበቅ ተግባር ነው ሲሉ አስገነዝበዋል።
#Ethiopia
#Development
#Corridor