በአውሮፓ ሀገራት የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ስሎቫኪያን የገጠመችው ጀርመን 2ለ0 ተሸንፋለች። ለስሎቫኪያ ዴቪድ ሀንኮ እና ዴቪድ ስትሬሌክ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
በዚሁ በምድብ አንድ ሰሜን አየርላንድ ሉክዘንበርግን 3ለ1 አሸንፋለች። በምድብ አምስት የምትገኘው ስፔን ከሜዳዋ ውጪ ቡልጋሪያን 3ለ0 ማሸነፍ ችላለች። ሚካኤል ኦያርዛባል ፣ ማርክ ኩኩሬያ እና ሚካኤል ሜሪኖ የስፔንን ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል።
በዚሁ ምድብ የተደለደለችው ተርኪዬ ጆርጂያን 3ለ2 አሸንፋለች። ቤልጂየም ሊችተንስታይንን አስተናግዳ 6ለ0 ረታለች። በሜዳዋ ፖላንድን ያስተናገደችው ኔዘርላንድ 1ለ1 ተለያይታለች። ከፍተኛ ብልጫ ወስዳ ለተጫወተችው ኔዘርላንድ ዴንዘል ዱምፍሪስ ሲያስቆጥር ለፖላንድ ማቲ ካሽ ኳስ እና መረብን አገናኝቷል።
በሸዋንግዛው ግርማ