የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለሚገኙ ወጣቶች ዘርፈ ብዙ የስራ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን በክልሉ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባባሪያ ፅ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ለሜሳ ኔኖ ጠቁመዋል።
በክልሉ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባባሪያ ፅ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ለሜሳ ኔኖ ለኤ ኤም ኤን ኤፍ ኤም 96.3 ሬድዮ እንደገለፁት፤ የግድቡን መጠናቀቅ ተከትሎ ወጣቶች በዓሳ ማስገር፣ በጀልባ ስራ፣ ጀልባ በመቅዘፍ ሥራና በሌሎች የስራ መስኮች የስራ እድል እየተፈጠረላቸው ስለመሆኑ ተናግረዋል።
በሌላ መልኩ የግድቡ መጠናቀቅ በክልሉ የኤሌክትሪክ ሀይል ባልተዳረሰባቸው አካባቢዎች ተደራሽ ለማድረግና ለቱሪዝም ፍሰቱ መጨመር ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተገልጿል።
የግድቡን መጠናቀቅ ተከትሎ ለሚኖረው የምርቃት ሥነ ሥረዓት ህዝቡ ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅቶችን እያደረገ እንደሚገኝ ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
በሰላማዊት ተስፋዬ