ጳጉሜን 1 ኢትዮጵያውያን በቁርጠኝነትና በአንድነት ሀገራቸውን ከፍታ ላይ ለማድረስ የሚያስችላቸውን የጽናት መንፈስ የሚያድሱበት መሆኑ ተገለፀ

You are currently viewing ጳጉሜን 1 ኢትዮጵያውያን በቁርጠኝነትና በአንድነት ሀገራቸውን ከፍታ ላይ ለማድረስ የሚያስችላቸውን የጽናት መንፈስ የሚያድሱበት መሆኑ ተገለፀ

AMN – ነሐሴ 30/2017 ዓ.ም

የጽናት ቀን ተብሎ የተሰየመው ጳጉሜን 1 ኢትዮጵያውያን በቁርጠኝነትና በአንድነት ሀገራቸውን ከፍታ ላይ ለማድረስ የሚያስችላቸውን የጽናት መንፈስ የሚያድሱበት መሆኑን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የቀኑ አከባበርን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ፤ ቀኑ በመከላከያ ሚኒስቴር፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አስተባባሪነት በተለያዩ መርሀ ግብሮች ይከበራል ብለዋል።

ከእነዚህ መርሀ ግብሮች መካከልም የጽናት ሸማኔዎች የተሰኘ ዶክመንተሪ ፊልም፣ ዲጂታል አውደርዕይን ጨምሮ የጽናትን ሀገራዊ ዋጋ የሚያስገነዝቡ ዝግጅቶች ይካሄዳሉ ብለዋል ሚኒስትሯ።

የደህንነት ተቋሟችንን ለማዘመን የተሄደበት ርቀት እና የተመዘገቡ አስደናቂ ድሎች የጽናት መገለጫ ሆነው የሚቀርቡበት እንደሆነም ነው ሚኒስትሯ ያነሱት።

ቀኑ የማያቋርጥ የስኬትና የድል መሰረት የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚወደስበት፤ ለጸጥታና ደህንነት መስኮች ለተመዘገበው ስኬት ዋጋ የሚሰጥበት ነው ያሉት ሚኒስትሯ፤ ከቀኑ 5:30 ላይም ሁሉም ባለበት ቆሞ የኢትዮጵያን መዝሙር ይዘምራል ብለዋል።

የሀገሪቱ ሚዲያዎችም በዚሁ ሰዓት ብሄራዊ መዝሙርን ይለቃሉ ነው ያሉት።

ጳጉሜን 1 “ጽኑ መሰረት ብርቱ ሀገር” በሚል መሪ ሀሳብ ይከበራል፡፡

በፍቃዱ መለሰ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review