በኮሪደር ልማት በተሰራ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር ላይ የመጸዳጃ ቤት ፍሳሽ የለቀቀዉ ሆቴል 300 ሺህ ብር ተቀጣ

You are currently viewing በኮሪደር ልማት በተሰራ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር ላይ የመጸዳጃ ቤት ፍሳሽ የለቀቀዉ ሆቴል 300 ሺህ ብር ተቀጣ

AMN ነሃሴ 30/2017 ዓ.ም

በኮሪደር ልማት በተሰራ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር ላይ የመጸዳጃ ቤት ፍሳሽ የለቀቀዉ ሆቴል 300 ሺህ ብር መቀጣቱን የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 የሚገኘዉ አምሮኝ ሆቴል በምሽት ጨለማን ተገን በማድረግ የመጸዳጃ ቤት ፍሳሽ በኮሪደር ልማት በተሰራው የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር በመልቀቁና በማበላሸቱ 300ሺህ ብር መቀጣቱን የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታዉቋል፡፡

የሆቴሉ ሃላፊዎችና ሰራተኞች የመጸዳጃ ቤት ፍሳሽን በጄኔሬተር ፓምፕ በመሳብ ወደ ፍሳሽ ቱቦ ሲለቁ መገኘታቸውን ባለስላጣኑ አስታዉቋል፡፡

የከተማ መስተዳድሩ መዲናዋን ለማልማትና ለማሳመር ቀንና ሌሊት በሚሰራበት በዚህ ሰዓት እንደዚህ አዓነት የደንብ መተላለፍ የሚፈፅሙ ግለሰቦችና ተቋማት ላይ የሚወሰደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በላከዉ መረጃ አስታዉቋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review