ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል በመገኘት ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከተውጣጡ ተወካዮች ጋር የቅድመ ምክክር መድረክ በመቀሌ አካሄደ

You are currently viewing ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል በመገኘት ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከተውጣጡ ተወካዮች ጋር የቅድመ ምክክር መድረክ በመቀሌ አካሄደ

AMN ነሃሴ 30/2017

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል በመገኘት ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ተወካዮች የተሳተፉበት የቅድመ ምክክር መድረክ በመቀሌ አካሄዷል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር መላኩ ወልደማሪያም፥ የኢትዮጵያን ከፍታ ለማረጋገጥ በምክክር ችግሮችን በመፍታት እጅ ለእጅ ተያይዞና ልብ ለልብ ተገናኝቶ መጓዝ ይገባል ብለዋል።

በመሆኑም በሀገራዊ ምክክሩ የተፈጠረውን ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም በምክክር ሀገራዊ ችግሮችን በዘላቂነት መፍታት ይገባል ብለዋል።

በዚህም መሰረት በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለው የቅድመ ምክክር መድረክ ለዚሁ ስኬት ጥሩ መሰረት የሚያኖር መሆኑን ገልፀዋል።

ለችግሮች ሁሉ ቁልፉ መፍትሄ ምክክር በመሆኑ እድሉን በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ ኮሚሽነሩ አስገንዝበዋል።

የመድረኩ ተሳተፊዎችም ሀገራዊ ችግሮችን በምክክር በዘላቂነት ለመፍታት ዝግጁ ስለመሆናቸው ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ፥ በትግራይ ክልል የምክክር ሂደት ለመጀመርና ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ቀደም ሲል ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር ውይይት መደረጉን መግለፃቸው ይታወሳል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review