ኢትዮጵያውያን የአዲስ አመት በዓላቸውን በደማቅ ባህላዊ ስርዓት ሲቀበሉ ማየት ያስደስታል ሲሉ አምባሳደር ኤርቨን ማሲንጋ ገለጹ

You are currently viewing ኢትዮጵያውያን የአዲስ አመት በዓላቸውን በደማቅ ባህላዊ ስርዓት ሲቀበሉ ማየት ያስደስታል ሲሉ አምባሳደር ኤርቨን ማሲንጋ ገለጹ

AMN- ነሐሴ 30/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በአሜሪካ ኤምባሲ ያቀረቡት የአዲስ ዓመት የኪነጥበብ ስራ የሁለቱን ሀገራት የባህል ትስስር እንደሚያጠናክረው ተገለጸ።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቨን ማሲንጋ መጪውን የኢትዮጵያውያን የ2018 ዓ.ም አዲስ አመት በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት አስመልክቶም የራስ ቴአትር የኪነጥበብ ሙያተኞች በአሜሪካ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ባህላዊ ትርኢት አቅርበዋል።

በዚሁ ወቅት አምባሳደር ኤርቨን ማሲንጋ ኢትዮጵያውያን የአዲስ አመት በዓላቸውን በደማቅ ባህላዊ ስርዓት ሲቀበሉ ማየት ያስደስታል ብለዋል።

አሜሪካም ኢትዮጵያ የብልጽግና ተስፋዋን ለማሳካት በምታደርገው ጥረት አጋርነቷን አጠናክራ እንደምትቀጥል ያረጋገጡት አምባሳደሩ ፤ የራስ ቴአትር የኪነጥበብ ሙያተኞች በአሜሪካ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ላቀረቡት የኢትዮጵያዊያን ውብ ባህላዊ የኪነጥበብ ትርኢት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ኢትዮጵያውያን መጪውን አዲስ አመታቸውን በአብሮነት እና በብሩህ ተስፋ እንዲቀበሉትም ምኞታቸውን የገለጠዑ ሲሆን ፤ አዲሱ አመት የሁለቱ አገራት ጠንካራ ወዳጅነት ተጠናክሮ የሚቀጥልበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ነብዩ ተድላ በበኩላቸው ኢትዮጵያና አሜሪካ የጠበቀ ወዳጅነት ያላቸው አገራት መሆናቸውን ተናግረዋል።

የራስ ቴአትር የኪነጥበብ ሙያተኞች በአሜሪካ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ያቀረቡት ውብ ባህላዊ ትርኢትም የሀገራቱን ወዳጅነት የሚያጠናክር መሆኑን ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review