የተለያዩ ሀገራት መሪዎች የ2ተኛው የአፍሪካ-ካረቢያን ማህበረሰብ የመሪዎች ጉባኤ ለማሳተፍ ወደ አዲስ አበባ በመግባት ላይ ናቸው፡፡
የግሪናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ዲክን ሚሸል፣ ለ2ተኛው የአፍሪካ-ካረቢያን ማህበረሰብ ጉባኤ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ሚኒስትሩ፣ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በተመሳሳይ የሰይንት ኪትስ እና ኔቪስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ቴራንስ ድሩ አዲስ አበባ አበባ ገብተዋል።
የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጅነር ሀብታሙ ተገኝ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላም ማረፊያ ሲደርሱ አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡