“የኢትዮጵያ አየር ሃይል ቴክኖሎጂያዊ አቅሙን ያለማቋረጥ እያሳደገ መሆኑ የሚያኮራ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ተናገሩ

You are currently viewing “የኢትዮጵያ አየር ሃይል ቴክኖሎጂያዊ አቅሙን ያለማቋረጥ እያሳደገ መሆኑ የሚያኮራ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ተናገሩ

‎AMN – ጳጉሜን 1/2017 ዓ/ም

“እኛ ጦርነት አንፈልግም፤ የግድ ከመጣብን ግን የጦርነት ወሳኝ አቅም የሆነው አየር ሃይላችን ራሱን በቴክኖሎጂ ያለማቋረጥ እያሳደገ መምጣቱ በእጅጉ የሚያኮራ ነው” ሲሉ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።

‎ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን ጨምሮ ከከፍተኛ የሠራዊቱ አመራሮች ጋር የኢትዮጵያ አየር ሃይልን ከጎበኙ በኋላ ነው።

‎ሰው ላይ ከተመሰረተ ይልቅ ቴክኖሎጂያዊ የውጊያ አቅም መፍጠር ላይ ማተኮሩ ፋይዳው የጎላ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ እንደሀገር የመከላከያ ሃይላችንን በማጠናከር ረገድ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።

በጉብኝቱ በአየር፣ ከአየር ወደ ምድር እና ከምድር ወደ አየር ውጊያዎች አስተማማኝ አቅም ስለመገንባቱ የገለጹት የአየር ሃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ከተቋማዊ ሪፎርም ወዲህ አየር ሃይልን በኢትዮጵያ ልክ እያገዘፍን እንገኛለን ብለዋል::‎

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review