ኢትዮጵያ ዘላቂ እና የማይበገር የጤና ስርዓት ለመገንባት ያለመ ህዝብን ያማከለ የጤና አገልግሎት አቅርቦትን ተግባራዊ እያደረገች መሆኑን አቶ አደም ፋራህ ገለፁ

You are currently viewing ኢትዮጵያ ዘላቂ እና የማይበገር የጤና ስርዓት ለመገንባት ያለመ ህዝብን ያማከለ የጤና አገልግሎት አቅርቦትን ተግባራዊ እያደረገች መሆኑን አቶ አደም ፋራህ ገለፁ
  • Post category:ጤና

AMN ጳጉሜን 1/2017

ኢትዮጵያ ዘላቂ እና የማይበገር የጤና ስርዓት ለመገንባት ያለመ ህዝብን ያማከለ የጤና አገልግሎት አቅርቦትን ተግባራዊ እያደረገች መሆኑን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ገለፁ።

ሁለተኛው የአፍሪካ – ካረቢያን የጤና ሚኒስትሮች ስብሰባ “በጋራ ወደፊት፣በአንድ ድምፅ በአንድ ዓላማ” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ነው።

በስብሰባው በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህን ጨምሮ የተለያዩ አገራት የጤና ሚኒስትሮች ተገኝተዋል።

ኢትዮጵያ ዘላቂና የማይበገር የጤና ስርዓት ለመገንባት ህዝብን ያማከለ እና ዘመኑን የዋጀ የጤና አገልግሎት አሰጣጥን ተግባራዊ እያደረገች መሆኑን አንስተዋል። በመድረኩ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በዓለም የጤና ስርዓት እና አቅርቦት ላይ ያሳደረውን ተግዳሮት አንስተዋል።

መሰል ወረርሽኞችን ለመከላከል እና ለመግታት አፍሪካ እና ካሪቢያን የህዝቦቻቸውን ጤና እና ደህንነት ለመጠበቅ ያላቸውን አቅም ማጠናከር አለባቸው ብለዋል።

ከክትባት ምርት እስከ መድሀኒት አቅርቦት ጠንካራ ስራ በመስራት የጤና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ አስረድተዋል።

በጤና አገልግሎት ተደራሽነት ራሳችንን ለመቻል የጋራ ቁርጠኝነትን ማሳደግ አለብን ያሉት የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም፤ መሠረታዊ የሆነውን የጤና አገልግሎት በበቂ ሁኔታ ለዜጎች ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባም ተናግረዋል።

ሁለንተናዊ የጤና ሽፋን ማሳደግ ለዘላቂ ልማት ግብ መሳካት ወሳኝ ሚና እንዳለው ነው የገለፁት።

በተዳከመ የጤና ስርዓት የበለፀገ ኢኮኖሚ መገንባት እንደማይቻል አውስተው፤ በመጀመሪያ ደረጃ የጤና እንክብካቤ ላይ ኢንቨስት ማድረግ ይገባል ብለዋል።

የማህበረሰብ አቀፍ የጤና ባለሙያዎችን በማብቃት እና የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን በመጠቀም ፍትሃዊ፣ ተመጣጣኝ እና ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለእያንዳንዱ ዜጋ በፍትሃዊነት ማዳረስ እንደሚቻል አስረድተዋል።

ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት የእናቶች፣ የጨቅላ የህፃናት ጤናን በማሻሻል ረገድ አስደናቂ እድገት መመዝገቡን አንስተው የእናቶች ሞት በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል ማለታቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ቀጣይነት ያለው የመንግስት ቁርጠኝነት፣ በጤና አጠባበቅ መሠረተ ልማት ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ፣ አስፈላጊ አገልግሎቶችን ማስፋፋት እና ጥራት ያለው አገልግሎትን ለማህበረሰብ በማድረስ እንደሚሆን ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review