በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ የተገነባው የኢትዮጵያ ባህር ኃይል የስልጠና ማዕከል በክቡር የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በዛሬው ዕለት ተመርቋል።
ኢትዮጵያ የቀደመ የቀይ ባህር ስመ ገናናነቷን ለመመለስ የባህር በር ባለቤት ከመሆን ጀምሮ ዘረፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራች ትገኛለት።
የነዚህ ጥረቶች አካል የሆነው የባህር ኃይል ስልጠና ማዕከልም ለምረቃ የበቃው የዕዞች፣የኃይሎቸ ፣የዋና መምሪያ ኃላፊዎችና በተዋረድ የሚገኙ የሰራዊታችን አዛዦች በተገኙበት ነው።
የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄነራል ደስታ አብቸ በመርከብ ቅርፅ የተገነባው የስልጠና ማዕከሉ በሁለት አመት ተኩል መጠናቀቁን ገልፀዋል።
የባህር ኃይል የስልጠና ማዕከል የተገነባው በኛው ወታደር ኢንጅነሮች እና ሙያተኞ መሆኑንም ተናግረዋል ።
ሌተናል ጄነራል ደስታ እንዳሉት ማዕከሉ የሰራዊት መኖሪያ ህንፃዎችን ፣መማሪያ ክፍሎችን ፣በኤሌክትሮ መካኒክ የሚሰራ መመገቢያ አዳራሽ ፣አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ስታዲዬም እና ሌሎችንም ግንባታዎች አካቶ ይዟል።
የስልጠና ማዕከሉ ደረጃውን የጠበቀ የውስጥ ለውስጥ አስፓልት እንደተገነባለት የተናገሩት ጄኔራል መኮንኑ ማሰልጠኛው ደረጃውን በጠበቀ የግንብ አጥር መታጠሩንም ገለፀዋል።
ግቢውን በአረንጓዴ አትክልቶች ውብ ማራኪና ሳቢ ማድረግ መቻሉን ከሃገር መከላከያ ሠራዊት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።