ፀረ-ሠላም ኃይሎች የከተማዋን ፀጥታ ለማደፍረስ ቢንቀሳቀሱም በፀጥታ ተቋማት አመራሮች፤ አባላት እና በነዋሪው ተሳትፎ የከተማዋን ሠላምና ደህንነት ማጽናት መቻሉ ተገለጸ

You are currently viewing ፀረ-ሠላም ኃይሎች የከተማዋን ፀጥታ ለማደፍረስ ቢንቀሳቀሱም በፀጥታ ተቋማት አመራሮች፤ አባላት እና በነዋሪው ተሳትፎ የከተማዋን ሠላምና ደህንነት ማጽናት መቻሉ ተገለጸ

AMN ጳጉሜ 1 ቀን 2017 ዓ/ም

ፀረ-ሠላም ኃይሎች የከተማዋን ፀጥታ ለማደፍረስ ቢንቀሳቀሱም በፀጥታ ተቋማት አመራሮች፤ አባላት እና በነዋሪው ተሳትፎ የከተማዋን ሠላምና ደህንነት ማጽናት መቻሉ ተገልጿል፡፡

“ጳጉሜን 1 የጽናት ቀን” ጽኑ መሰረት ብርቱ ሀገር በሚል መሪ ቃል ቀኑ በአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ተከብሯል፡፡

በዝግጅቱ ላይ የጠቅላይ መምሪያው አዛዥ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ባስተላለፉት መልዕክት ልዩ ልዩ ጫናዎችን ተቋቁመን እንዲሁም ብዙ ውጣ ውረዶችን አልፈን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን አጠናቀን ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ ባለንበት በዚህ ወቅት የጽናትን ቀን ማክበራችን ቀኑን የተለየ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

ለውጡን ተከትሎ ፀረ-ሠላም ኃይሎች የከተማዋን ፀጥታ ለማደፍረስ ቢንቀሳቀሱም ለቆሙለት ዓላማ በጽናት በቆሙ የፀጥታ ተቋማት አመራሮችና አባላት እንዲሁም በነዋሪው ተሳትፎ የከተማችንን ሠላምና ደህንነት ማጽናት መቻሉን ገልፀዋል፡፡

ብርቱ ሀገር መገንባት የሚቻለው ሁሉም በተሰማራበት የስራ መስክ ኃላፊነቱን በአግባቡ ሲወጣ መሆኑን አዛዡ ተናግረው የከተማዋን ሠላምና ደህንነት ለማፅናት መላው የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አመራሮችና አባላት እንደሁልጊዜው ኃላፊታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ወታደርና ጽናት ጥብቅ ቁርኝት እንዳላቸው የተናገሩት የፖሊስ አባላት በሁለም ዘርፍ ብርቱ ሀገር ለመፍጠር መንግስት የጀመራቸው ተግባራት ስኬታማ እንዲሁኑ እንደ ዜጋ የድርሻቸውን እንደ ፖሊስ ደግሞ ግዳጃቸውን ለመወጣት ዝግጁ ነን መሆናቸዉን መናገራቸዉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በላከዉ መረጃ አስታዉቋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ የማርቺንግ ባንድ ቀኑን አስመልክቶ ሀገራዊ ይዘት ያላቸው ሙዚቃዎች አቀርቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review