የኢትዮጵያ ፅናት

You are currently viewing የኢትዮጵያ ፅናት

AMN- ጳጉሜ 03/2017

የኢትዮጵያ ፅናት በታሪክ ሂደት ውስጥ በብዙ መልኩ የሚገለጽና ተግዳሮቶችን ድል አድርጎ ለማለፍ ሁነኛ የአንድነት መሳሪያ ሆኖ ይታያል፡፡

ይህ ፅናት የህዝቡን ከውስጥና ከውጭ የሚመጡ ችግሮችንና ተግዳሮቶችን የመቋቋም አቅም ያሳያል።የኢትዮጵያ ፅናት ከሌላው የዓለም ክፍል በተለየ መልኩ ሊታይ የሚችልበት የራሱ መገለጫዎችንም የያዘ ነው።

ከኤ ኤም ኤን ጋር ቆይታ ያደረጉት የባህልና ታሪክ ተመራማሪው ፕሮፌሰር አህመድ ዘካሪያ፣ የኢትዮጵያ ፅናት በፅኑ አለት ላይ የተመሠረ ቢሆንም ሶስት ዋና ዋና ነጥቦችን አንስተዋል።

ኢትዮጵያ በሺህ አመታት ታሪኳ ውስጥ ብዙ ውጣ ውረዶችን፣ የውስጥ ግጭቶችን፣ ረሀብን እና የውጭ ወራሪዎችን ተቋቁማ ለዛሬ ደርሳለች የሚሉት ፕሮፌሰሩ፣ ከአድዋ ድል እስከ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ድረስ የሀገሪቱ ህዝብ በጋራ ወረራዎችን የመከተበት ፅናት ሀገራዊ ማንነቷን እንዳታጣ ትልቅ ሚና ተጫውቷል በማለት ታሪካዊ ፅናት አብራርተዋል።

በሁለተኛ ደረጃ ኢትዮጵያ ከድህነት ለመውጣት ለረጅም ጊዜ ስትታገል የኖረች ሀገር ነች፣ይህ ትግል የህዝቡን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሚያደርገውን የማያቋርጥ ጥረት ያሳያል።በግብርናው ዘርፍ የሚታየው ፅናት፣ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ዋና መሠረት ሆኖ እያገለገለ መሆኑን በአብነት ይጠቅሳሉ፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ለዘመናት በአንድነትና በሰላም አብረው ኖረዋል የሚሉት ፕሮፌሰር አህመድ፣ ይህ አብሮ የመኖር ፅናትና ትዕግስት ለሀገሪቱ ሰላም እና መረጋጋት አስፈላጊ እንደመሆኑ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ የመፍታት ፍላጎት እንደሚያመላክት አንስተዋል።

በጥቅሉ የኢትዮጵያ ፅናት በሀገሪቱ ውስጥ ለሚከሰቱ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ምላሽ በመስጠት፣ የሚያጋጥሙ መሰናክሎችን ፀንቶ የማለፍ እና ወደፊት የመራመድ ፍላጎት አመላካች ነው፡፡ ለዚህም በቅርቡ ለምረቃ የሚበቃው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ሁነኛ ማሳያ ነው ሲሉ አክለዋል።

አሁን ላይ ፅናታችንን ለለውጥና ለልማት በማድረግ መነሳሳት ይኖርብናል የሚሉት ፕርፌሰር አህመድ ዘካሪያ፣የትላንት ፅናታችንን መማሪያ በማድረግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

የአረንጓዴ አሻራ፣የገበታ ለሀገር፣የስንዴ ምርታማት ፣የአፈር ማዳበሪያ ምርት ፋብሪካ ግንባታ እንዲሁም የማዕድንና ቱሪዝም ዘርፍን ጨምሮ ያሉ ፀጋዎች የኢትጵያን ከፍታ የሚያረጋግጡ እንደመሆናቸው በአንድነት በመፅናት ለዓለም ምሳሌ የምንሆንበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡

ፅናት የሀገሪቱን ታሪካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ መሰናክሎችን ለመቋቋም ሁልጊዜም ትልቅ ሚና ያለው ሲሆን ጷጉሜን አንድ ፅኑ መሠረት ብርቱ ሀገር በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ሁነቶች ይከበራል።

በሚካኤል ህሩይ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review