የተቋሙን ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ በጋራ መስራት እንደሚጠይቅ የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ገለፀ

You are currently viewing የተቋሙን ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ በጋራ መስራት እንደሚጠይቅ የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ገለፀ

AMN ጳጉሜን 1/2017

የኢንስቲትዩቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ደሳለኝ ጣሰው የተቋሙን ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነት ለማሳደግና በጋራ መስራት በጋራ መዘጋጀት አለብን ብለዋል።

ኢንስቲትዩቱ የሚሰጣቸው የሥልጠና ፣ የምክር እና የጥናትና ምርምር እና ሌሎችም አገልግሎቶች ዘመናዊ እና ለሀገር ጠቀሚታ ያላቸው እንዲሆኑ የተቋሙ ባለሙያዎች ሚና የላቀ መሆኑንም ዋና ስራ አስፈፃሚው ገልጸዋል።

ኢንስቲትዩቱን እንደ አዲስ ለማዋቀር በአዋጅ ቁጥር 5313/2017 ለኢንስቲትዩቱ የተሰጠው ሀገራዊ ኃላፊነት በጋራ ለመወጣትም እያንዳንዱ ባለሙያ ድርሻውን መውጣት እንዳለበት አቶ ደሳለኝ ተናግረዋል።

የኢንስቲትዩቱን የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ በደብረዘይት / ቢሾፍቱ / የስልጠና ማዕከል ውይይት አካሄዷል።

በውይይቱ የተሳተፉት የተቋሙ ሰራተኞችም ተቋሙን በአፍሪካ እውቅና ያለው የላቀ የሥራ አመራር ልማትና የመማር ማዕከል ለማድረግ የያዘውን ራዕይ ለማሳካት ዘመኑ የሚፈልገውንና አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል ።

በዳንኤል መላኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review