ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ብዝኃነት ያለንን የጸጋ ብዛት የሚያመለክት ነው ሲሉ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የኅብር ቀንን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት ብዝኃነት የኢትዮጵያ ጌጥ ነዉ ብለዋል።

ኢትዮጵያ በብዙ ጸጋዎች የተሞላች ሀገር ናት፡፡ እነዚህ ጸጋዎቿ የተለያዩ ሳይሆኑ ልዩ ልዩ ናቸው፡፡ የባህል፣ የቋንቋ፣ የታሪክ፣ የሥልጣኔ፣ የእምነት፣ የጾታ፣ የአመለካከት፣ ወዘተ. ብዝኃነት ያለንን የጸጋ ብዛት የሚያመለክት ነው፡፡ ብዝኃነት የኢትዮጵያ ታሪኳ እና መልኳ ነው ሲሉ ገልጸዋል።