የጋምቢያ ምክትል ፕሬዝዳንት ሞሃመድ ጃሎ እና የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ሁሴን አብዱልቃድር ፣ የጋና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሙኤል ኦኩዴዜቶ አብላክዋ በአፍሪካ-ካረቢያን ማህበረሰብ ጉባኤ እና በአፍሪካ አየር ንብረት ጉባኤ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል ።
በቦሌ አለምአቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሰላም ሚኒስትር አቶ መሀመድ እድሪስ እና ሌሎች ከፍተኛ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል ማድረጋቸዉን ከዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።