የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከጉባኤዎቹ ቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ እስከ ፍፃሜ ድረስ በቴክኖሎጂ የታገዘ የሰው ኃይል ስምሪት ማድረጉን አስታወቀ

You are currently viewing የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከጉባኤዎቹ ቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ እስከ ፍፃሜ ድረስ በቴክኖሎጂ የታገዘ የሰው ኃይል ስምሪት ማድረጉን አስታወቀ

AMN – ጳጉሜን 2/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀችው 2ኛው የአፍሪካ አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን ጨምሮ የአፍሪካ-ካሪቢያን መሪዎች ጉባኤ እና በቀጣይም የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚካሄድ ይታወቃል።

በመሆኑም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታና ደኅንነት ኃይሎች ጋር በመቀናጀት ጉባኤዎቹ ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲካሄዱ ለማድረግ ከጉባኤዎቹ ቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ እስከ ፍፃሜ ድረስ በቴክኖሎጂ የታገዘ የሰው ኃይል ስምሪት ማድረጉን ለኤ ኤም ኤን በላከው መግለጫ አስታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪ የትራፊክ ፍሰቱን ለማሳለጥ በርካታ የትራፊክ ፖሊሶችም ስምሪት ወስደው የትራፊክ ቁጥጥርና ክትትል እንደሚያደርጉ እየገለፀ፤ መንገዶች እንዳይጨናነቁ ኅብረተሰቡም የድርሻውን እንዲወጣ ጠይቋል።

ኅብረተሰቡ እስከአሁን እያሳየ ላለው ድጋፍ ምስጋውን እያቀረበ በቀጣይ ለሚኖሩ አጠቃላይ የፀጥታና የትራፊክ ደንብ ለማስከበር በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review