በህብር ቀን ለ500 ሺህ የከተማዋችን ነዋሪዎች ማዕድ አጋርተናል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልፀዋል።
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት፤ በክረምቱ ወራትም ምንም ጧሪ፣ ደጋፊ የሌላቸው አቅመ ደካሞችን፤ የአገር ባለውለታዎችን እና በዝቀተኛ ገቢ የሚተዳደሩ 156 ሺህ ያህል የህብረተስብ ክፍሎችን ስንደግፍ ቆይተናል ብለዋል።
ወገኖቻችን በጊዜያዊ ችግሮች እንዳይጎዱ በተለያዩ መልኩ ለመደገፍ እየሰራን በዘላቂነት ከድህነት ለመውጣት 24/7 ዘላቂ የልማት ሥራዎችን እየሰራን እንገኛለን ሲሉ ገልፀዋል።

በመደጋገፍ ፤ በመረዳዳት ለማህበራዊ ችግር ተጋላጮች የምናደርገውን ድጋፍ ማጠናከር ይገባናል ያሉት ከንቲባዋ፤ ሁልጊዜ ከጎናችን ሆናችሁ ካላችሁ ለምታካፍሉ፣ ለመስጠት ለማትሳሱ ባለሀብቶች፣ ለከተማችን ወጣቶች ድጋፍ በተደረገላቸው ወገኖቻችን ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ማዕድ የማጋራት መርሃ ግብሩ በሁሉም ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች በተመሳሳይ መልኩ እየተከናወነ ይገኛል፡፡