በሁለተኛዉ የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ የሀገራት መሪዎችን ጨምሮ ከ25 ሺ በላይ አፍሪካዊያን እንደሚሳተፉ የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡ ሁለተኛዉ የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ለማስተናገድ በተደረጉ ቅድመ ዝግጅቶች ዙሪያ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡
መግለጫዉን የሰጡት የኢፌዴሪ የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ለጉባኤዉ ስኬታማነት በቂ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል፡፡
ጉባኤዉ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ሚዛንን ለማስጠበቅ የምትወስዳቸዉ የአረንጓዴ አሻራ የታዳሽ ሀይል አጠቃቀም እና መሰል የተፈጥሮ ጥበቃ ልምዶቿን የምታጋራበት ይሆናል ብለዋል፡፡ ሁለተኛዉ የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ አፍሪካዊያን የጋራ አቋም የሚያንፀባርቁበት እንደሚሆንም ማኒስትሯ ገልፀዋል፡፡
በጉባኤዉ ላይ የሀገራት መሪዎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጨምሮ ከ25ሺ በላይ የሚመለከታቸዉ አካላት ይገኛሉ፡፡
በተመስገን ይመር