በአለም አቀፍ ደረጃ እያጋጠሙ ለሚገኙ ፈተናዎች የጋራ ድምጽ ማሰማት ይገባል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
የአፍሪካ ካሪቢያን ሀገራት ሁለተኛው ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
ጉባዔው እየተካሄደ የሚገኘው “ለአፍሪካውያንና ዘረ አፍሪካውያን የማካካሻ ፍትሕን ለመሻት አኅጉር ተሻጋሪ አጋርነት” በሚል መሪ ሐሳብ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በጉባዔው ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ዓለም እየተቀየረ መሆኑን ገልጸዋል። በአንድ ወቅት ችላ የተባሉ ድምጾች አሁን መሰማት እንደሚሹም አስገንዝበዋል።
በዚህ ወቅትም በተናጠል ሐሳብን ከመግለጽ ይልቅ፤አንድነት ኃይል መሆኑን በመገንዘብ በጋራ ድምጽ ማሰማት ይጠበቅብናል ሲሉ ገልጸዋል። ለዚህም ደግሞ እንደ የአፍሪካ ካሪቢያን ሀገራት ጉባዔ ያሉ መሰባሰቦች ወሳኝ መሆናቸውን ነው ያስገነዘቡት።
በመሆኑም በአለም አቀፍ ደረጃ እያጋጠሙ ለሚገኙ ፈተናዎች ምላሽ ለመስጠት የአህጉራዊ አንድነትን አስፈላጊነት መጠቆማቸዉን የዘገበዉ ኢዜአ ነዉ፡፡