ሼኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት በመሆን ቃለ መሀላ ፈፀሙ

You are currently viewing ሼኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት በመሆን ቃለ መሀላ ፈፀሙ

AMN-ጳጉሜን 2/2017

ሼኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ቃለ መሀላ ፈፅመዋል፡፡

ትላንት ጀምሮ በተካሄደው ምርጫ ጠቅላይ ም/ቤቱን ለ5 ዓመታት የሚመሩ ከፍተኛ አመራሮች እና ስራ አስፈፃሚ አባላት ታውቀዋል።

ሼኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት በመሆን በድጋሚ ተመርጠዋል።

“ምርጫችን በመስጂዳችን” በሚል መሪ ሀሳብ ከሰኔ 12 ጀምሮ በየመስጂዱ ምዝገባ ሲከናወን ቆይቶ፤ ከ13 ሚሊዮን በላይ የሚሆን ሰው ተመዝግቦ ከትግራይ ክልል ውጭ በመላው ሀገሪቱ ከነሃሴ 9 እስከ ነሃሴ 30 /2017 ዓ.ም ድረስ ድምፅ የመስጠት ሂደት ከተከናወነ በኋላ ከወረዳ ጀምሮ በየደረጃው ምክር ቤቶች ተመስርተው ለቀጣዩ እርከን ተወካዮች ተመርጠዋል።

በምርጫው ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ አካታች ለማድረግ ተሰርቶ፤ ከዑለማ ባሻገር ምሁራን ወጣቶች፣ ሴቶች እና የስራ ማህበረሰብ እንዲሁም የዲያስፓራ ማህበረሰብ አባላት በየዘርፋቸው ወኪሎቻቸውን መርጠዋል።

የምርጫ አስፈፃሚ ቦርዱ ይፋ ባደረገው መሰረትም ከነሃሴ 9 ጀምሮ “ምርጫችን በመስጂዳችን” በሚል መርህ ሲካሄድ የቆየው ታሪካዊው ምርጫ ከፍተኛ አመራሮቹን በመምረጥ ተጠናቋል።

በዚህ መሰረት:-

1- ሼኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ -ፕሬዝዳንት

2- ሼኽ አብዱልከሪም ሼኽ በድረዲን- ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት

3- ሼኽ ጁነይድ ሀምዛ-ምክትል ፕሬዝዳንት

4- ሼኽ ሀሚድ ሙሳ- ምክትል ፕሬዝዳንት

5- ዑስታዝ ተምኪን አብዱላሂ- ዋና ፀሀፊ (ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ) ምሁር

6- ሸይኽ አሚን ኢብሮ-የስራ አስፈፃሚ አባል (ከድሬዳዋ )

7- ዶ/ር ሙሐመድ ሳሊህ – የስራ አስፈፃሚ አባል (ከኦሮሚያ)

8- ሸይኽ ሙሐመድ አሚን አያሽ – የስራ አስፈፃሚ አባል (ከሐረሪ)

9- ሸይኽ ሙሐመድ አህመድ ያሲን የስራ አስፈፃሚ አባል (ከአፋር)

10- ሸይኽ ኢድሪስ ደጋን- የስራ አስፈፃሚ አባል (ከአማራ ክልል)

11- ዑስታዝ ፋሪስ ግርማ- የስራ አስፈፃሚ አባል (ከደቡብ ምዕራብ) ምሁር

12- ዑስታዝ ፋይሰል ኢማም – የስራ አስፈፃሚ አባል (ከጋምቤላ) ምሁር

13- ዑስታዝ ፋሪስ ጀማል – የስራ አስፈፃሚ አባል (ከደቡብ ኢትዮጵያ) ምሁር እና

14- ዑስታዝ ሽኩር ቃሲም- የስራ አስፈፃሚ አባል (ከሲዳማ ክልል) ምሁር

15 ኢንጅነር አንዋር ሙስጠፋ (ትግራይ) ምሁር ሆነው ተመርጠዋል።

በተጨማሪም 7 አባላት ያለው የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዑለማ ጉባኤ አባላት የተመረጡ ሲሆን

በዚሁ መሰረት፦

1 ሼኽ አሊ መሀመድ- ሰብሳቢ

2 ማህሙድ ሁሴን( ዶ/ር)- ምክትል ሰብሳቢ

3- መሀመድ ከማል(ዶ/ር)- ጸሀፊ

4 ሼኽ ኤልያስ አህመድ -አባል

5 ሼኽ አብዱሰላም አንዋር – አባል

6 ሼኽ ዚያድ አሊይ- አባል

7 ሼኽ አድናን መሀመድ -አባል

ሆነው ተመርጠዋል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱን ለቀጣይ አምስት አመታት እንዲመሩ ትላንት የተመረጡ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ በታላቁ አንዋር መስጂድ ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።

በአንዋር አህመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review