የአሸናፊነታችን፣ የመቻላችን ሚስጥር ህብረብሄራዊ አንድነታችን ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ባህልና ኪነ-ጥበብ ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሳው (ዶ/ር ) ተናግረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ባህልና ኪነ-ጥበብ ቢሮ አራት ኪሎ ኘላዛ ላይ በተለያዪ ኪነ ጥበባዊ ዝግጅቶች የጳጉሜን ሁለት የሕብር ቀንን በድምቀት አክብሯል፡፡
የቢሮው ሀላፊ ሂሩት ካሳው (ዶ/ር) በዝግጅቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የጳጉሜን ሁለት የህብር ቀን “ብዘሀነት የኢትዮጰያ ጌጥ” በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የአሸናፊነታችን፣ የመቻላችን ሚስጥር ህብረብሄራዊ አንድነታችን ነው ያሉት ሀላፊዋ፤ ብዝሀነታችን ዛሬም ትናንትም አሸናፊ እንድንሆን አድርጎናል ብለዋል።

የህብር ቀንን የምናከብረው በአዲስ አመት ዋዜማ በመሆኑ ህብረታችንን የተሻለ ነገን ለመስራት እንደመንደርደሪያ መጠቀም አለብን ሲሉ ተናግረዋል።
የአዲስ አመት መንደርደሪያ የጳጉሜ ወር፤ የተስፋ፣ የይቅርታ እና የሰላም እንዲሆን የምንመኝበት፤ የላቀ ለመስራት የምናቅድበት ነው ብለዋል።
የህብር ቀን በአራት ኪሎ እንብርት ላይ በብስክሌት ውድድር፣ በስኩተር እንቅስቃሴዎች ፣ በባህላዊ የበዓልና አገራዊ ሙዚቃዎች፣ ስዕል በመሳል እና በተለያዩ ዝግጅቶች ተካሂዷል።
ህብር ቀን የኢትጵያን ህብረብሄራዊ አድነትን በሚገልፅ እና በሚሳይ መንገድ የተከበረ ሲሆን፣ አዲስ አመት ዋዜማን የሚያደምቁ ዝግጅቶች ቀርበዋል።
በሔለን ተስፋዬ