ሁለተኛው የአፍሪካ አየር ለውጥ ጉባኤ ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀናት በአዲስ አበባ ይካሄዳል።
ጉባኤው “ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት መፍትሄዎችን ማሳለጥ፣ የአፍሪካን አረንጓዴ ልማት በፋይናንስ መደገፍ” በሚል መሪ ሀሳብ ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀናት በአዲስ አበባ ይካሔዳል።
ከዋናው ጉባዔ አስቀድሞ ባለፉት ጥቂት ቀናት ቅድመ ጉባዔዎቹ በተሳካ ሁኔታ መካሄዳቸውንና ለፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ ሀሳቦች መነሳታቸው ተገልጿል። ኢትዮጵያም የአየር ንብረት ለውጥ ችግርን በጋራ መከላከል የተሻለ ውጤት ለማምጣት ያላትን አቋም እና ያከናወነቻቸውን ተግባራት በጉባኤው ታንፀባርቃለች።
በጉባኤው አካባቢያዊ መፍትሄዎችን ከአህጉራዊ የአየር ንብረት ስትራቴጂዎች ጋር ማስተሳሰር በሚቻልበት ሁኔታዎች ላይ ምክክር ይደረጋል። አፍሪካውያን የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በቁርጠኝነት የሚሰሩበት የ”አዲስ አበባ ድንጋጌ ስምምነት”በጉባዔው እንደሚጸድቅ ይጠበቃል።
አፍሪካ በአየር ንብረት አስተዳደር ትክክለኛ ቦታ ለመያዝ የምታደርገውን ጥረት የሚያግዙ ውሳኔዎች ይተላለፋሉ ተብሎም ይጠበቃል። በጉባዔው የተለያዩ ሀገራት መሪዎችን ጨምሮ ከ25ሺ በላይ ተሳታፊዎች ይታደማሉ