ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዓላማችን ከአንድ ምዕራፍ ወደ ሌላ ምዕራፍ መሻገር ሳይሆን ከትናንት ዘለን ወደ ነገ መድረስ ነው ሲሉ ገለጹ

You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዓላማችን ከአንድ ምዕራፍ ወደ ሌላ ምዕራፍ መሻገር ሳይሆን ከትናንት ዘለን ወደ ነገ መድረስ ነው ሲሉ ገለጹ

AMN ጳጉሜን 3/2017

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ዓላማችን ከአንድ ምዕራፍ ወደ ሌላ ምዕራፍ መሻገር ሳይሆን ከትናንት ዘለን ወደ ነገ መድረስ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ የእመርታ ቀን: እመርታ ለዘላቂ ከፍታ በማለት ባስተላለፉት መልዕክት የወረስነው ዕዳ ብዙ፤ የምንጓዝበት መንገድ ረዥም፤ ሕዝባችንም ፍላጎት ሰፊ ነው፡፡ ቀስ በቀስ በሚደረግ የተለምዶ ጉዞ ወደምንፈልገው የብልጽግና ምእራፍ አንደርስም ብለዋል።

ያለን አማራጭ አንዳንድ እርከኖችን መዝለል ነው። ለዚህ ደግሞ ፈጠራና ፍጥነት ወሳኞች ናቸው። ከተለመደው መንገድ ወጣ ማለት፣ ከተለመደው ጊዜ በላይ መሥራት፣ ከተለመደው ዋጋ በላይ መክፈል ያስፈልገናል፡፡ ዓላማችን ከአንድ ምዕራፍ ወደ ሌላ ምዕራፍ መሻገር አይደለም፡፡ ከትናንት ዘለን ወደ ነገ መድረስ ነው በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review