ካርሎስ አልካራዝ የ2025 የዩ ኤስ ኤ ኦፕን ሜዳ ቴኒስ የወንዶች ነጠላ ውድድር ባለድል ሆኗል። የ22 ዓመቱ ስፔናዊ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በታደሙበት ጨዋታ ጣልያናዊውን ያኒክ ሲነር አሸንፏል።

አልካራዝ በአጠቃላይ ውጤት 3ለ1 በማሸነፍ ለሁለተኛ ጊዜ የዩ ኤስ ኦፕን ባለድል መሆን ችሏል። በአጠቃላይ ያሸነፋቸውን የግራንድ ስላም ብዛትም ስድስት አድርሷል። አልካራዝ ድሉን ተከትሎ የዓለም ቁጥር አንድነቱን ቦታ ይዟል።
ለበርካታ ሳምንታት ቀዳሚውን ስፍራ ይዞ የቆየው ያኒክ ሲነር ወደ ሁለተኛ ደረጃ ወርዷል።
በሸዋንግዛው ግርማ